ዜና

የአጊቱ ጉደታ አስከሬን አዲስ አበባ ገባ

Views: 208

ነዋሪነቷን በጣሊያን አድርጋ የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ አጊቱ ጉደታ መገደሏ ይታወሳል፤ በአሁኑ ጊዜ አስከሬኗ በክብር አዲስ አበባ ገባ ገብቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ቤተሰቦቿ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አስከሬኑን ተቀብለዋል፡፡

በጣልያኗ ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየል እያረባች የፍየል ተዋጽኦዎችንና የቆዳ ቅባቶችን በመሸጥ የጠንካራ ሠራተኛነት ተምሳሌት የነበረችው አጊቱ ጉደታ በሰራተኛዋ ለህልፈት መዳረጓ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ኢትጵያዊቷ አጊቱ ጉደታ በፈረንጆቹ 2010 ወደ ጣሊያን በስደት ማምራቷን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com