በመከላከያ ቁጥጥር ሥር የዋሉት እነ አባይ ወልዱ አዲስ አበባ ገቡ

Views: 85

የቀድሞውን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትን ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ አገር ለመበታተን ሲሰሩ ቁጥጥር ስር የዋሉ ጽንፈኛ የህወሓት የአመራር አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ኃይል በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ አገር ለመበታተን ሲሰሩ የነበሩ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላትን ለሕግ የማቅረብ ተልዕኮ እንደቀጠለ ነው።

በትናንትናው ዕለትም የቀድሞውን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ አሁን አዲስ አበባ ገብተዋል።

በቁጥጥር ሥር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ የገቡ የጁንታው አመራሮች፡-

1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ

2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ – የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ

3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ

4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ

የነበረ

5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ

6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና

ደህንነት ሃላፊ የነበረ

7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች

ናቸው።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com