በምዕራብ ወለጋ ዞን 8 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

Views: 51
  • ስድስት ደግሞ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በምዕራብ ወለጋ ዞን ስር ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በተደረገው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ስምንት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

በሕግ ማስከበር ስራው ስድስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና 87 ደጋፊዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ለሁለት ወራት በዞኑ በተደረገው የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ 265 የኦነግ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል፡፡

የኦነግ ታጣቂዎች ሲጠቀሙበት የነበረው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com