ቅምሻ ከወዲያ ማዶ፡- በኢንዶኔዥያ የመሬት መንሰራተት 11 ሰዎች ሲሞቱ 18 ሰዎች ቆሰሉ

Views: 49

በምዕራብ ኢንዶኔዥያ በከባድ ዝናብ ምክንያት የተከሰተው የመሬት መንሸራተት 11 ሰዎች ሲሞቱ 18 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ 14 ቱ ደግሞ በኢንዶኔዥያ ምዕራብ ጃቫ አውራጃ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ እና ማታ በደረሰው የመሬት መንሸራተት ወቅት በጭቃ ስር እንደተቀበሩ ታምኖ ነበር፡፡

ቅዳሜ ዕለት የኢንዶኔዥያ ብሔራዊ የአደጋ መከላከል ቦርድ ቃል አቀባይ ራዲቲያ ጃቲ በሰጡት መግለጫ አደጋው ከዋና ከተማው ጃካርታ በስተደቡብ ምስራቅ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ጃቫ ውስጥ በሲሃንጁአንግ መንደር ተከስቷል፡፡

ተጎጂዎችን የማፈላለግና የማዳን ሥራ በሚከናወንበት ወቅት በድንገት ሌሎች የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተከስተው በርካታ አዳኞችን ቀብረዋል ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com