ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ጉዳይ በውይይት እንድትፈታ ደቡብ ሱዳን አሳሰበች

Views: 69

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሱዳን ከድንበር ጋር ተይይዞ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጉዳይ፣ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ አሳሰቡ።

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል በሆኑት ሻምስ ል ዲን ካባሺ የተመራ ልዑክ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚህ ወቅትም በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ በዲፕሎማሲና በውይይት እንዲፈታ ነው ያሳሰቡት።

በቀጠናው ምንም አይነት ጦርነት አያስፈልግም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ሀገራቱ የድንበር ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት አለባቸው ብለዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com