ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት በከፊል መጀመሩን ተናገረ

Views: 193
ኢትዮ ቴሌኮም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሽራሮ፣ በማይፀብሪ እና በማይካድራ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሩን እወቁልኝ ብሏል፡፡
በአላማጣ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሩን ተናግሯል፡፡
በትግራይ የተጎዱ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች እንዳሉ የጠቀሰው ኢትዮ ቴሌኮም፣ የተጎዱትን መሠረተ ልማቶች ለመጠገንና መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት ጥገና ይደረጋል ብሏል፡፡
የኃይል አቅርቦትን ለማግኘት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር እየተሠራ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም ተናግሯል፡፡
በትግራይ ክልል ባለፈው 3 ሳምንት በነበረው ችግር ሳቢያ የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com