ዜና

ሰበር ዜና! መከላከያ ሠራዊት አዲግራትን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ መቀሌ እየገሠገሠ ነው

Views: 440

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ወደ መቀሌ እየገሠገሠ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መረጃ ማጣሪያ አሳወቀ።

“ዛሬ ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲግራትን ከህወሓት ጁንታ ነጻ ወጣች” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ገልጿል።

“የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ዛሬ በጠዋቱ የህወሓትን ጁንታ ኃይል ድል አድርጎ የአዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ ነጻ አውጥቶ ያጸና ሲሆን በፍጥነት ወደ መቀሌ እያመራ ነው” ብሏል።

ትናንት ማምሻውን ሠራዊቱ አክሱም፣ ዓድዋን እና አዲግራት ዙሪያን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወቃል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com