ዜና

‹‹የጽንፈኛው ህወሓት ቡድን ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እየተፍረከረከ ነው››

Views: 229

የጽንፈኛው ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች በነዳጅና መሠረታዊ አቅርቦት ችግር ተስፋ ቆርጠዋል፤ በምግብ እጥረት ለረሃብ ተዳርገዋል በዚህም ከየግንባሩ እየሸሹ እንዳሉ ተጠቆመ፡፡

የጽንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች እና ሚሊሻዎች በሎጂስቲክስና በምግብ አቅርቦት እጥረት ሳቢያ ለርሃብና እንግልት ከመዳረጋቸውም በላይ፣ መቀሌ ከመሸጉ አመራሮች በቂ ግንኙነትና ምላሽ እያገኙ እንዳልሆነ ምንጩን ጠቅሶ ኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ታጣቂዎቹ ከመቀሌ ከሚገኙ አለቆቻቸው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በተለይም ከመቀሌው ቡድን ጋር ግንኙታቸው ተቋዋርጧል፤ የነዳጅ አቅርቦትን ጨምሮ በበርካታ ችግሮች እየተሰቃዩ ነው” ብለዋል፡፡

መቀሌ የከተመውና ተስፋ የቆረጠው የህውሓት ጁንታ ‘ልዩ ኃይሉን’ እና ሚሊሻዎችን በመምራት መዋጋት አቅቶታል፡፡ በመሆኑም፣ የተራቡና መሪ አልባ ታጣቂዎች ከመሪዎቻቸው ጋር መጋጨታቸው አይቀሬ ነው ሲል ኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ጽንፈኛው ቡድን በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ ጥቃት ማደርሱን ተከትሎ በተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በርካታ ታጣቂዎች በማያምኑበት ውጊያ መሳታፋችን ትክክል አይደለም በሚል እጃቸውን ለሠራዊቱ እየሰጡ መሆናቸው ይታወቃል::

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com