ዜና

ም/ል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር ተወያዩ

Views: 182

ም/ጠ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር ተወያዩ። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ የቀጠናው ሀገራት መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማጽናት ጥረት እንዲደግፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት ለፕሬዚዳንቱ አድርሰዋል።

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር በነበራቸው ቆይታም በትግራይ እየተካሄደ ባለው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በዚሁ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉር ቅኝ ያልተገዛች ሀገር መሆኗን በማስታወስ፤ ይህም ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ኩራት መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሀገሪቷ ሰላም ለቀጠናው ወሳኝ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከስድስት በላይ በሚሆኑ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኡጋንዳ ለማሸማገል እንዳሰበችና ለዚሁ ሲባል የልዑካን ቡድን እንደሚጓዝ የሚያትትና በኢትዮጵያም ሆነ በኡጋንዳ ያልተሰበና ተቀባይነት የሌለው የሐሰት መረጃ በፅንፈኛው ቡድን ተፈብርኮ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በመሰራጨት ላይ እንዳለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com