ዜና

የህወሓት ድርጅቶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

Views: 280

በአዲስ አበባ ቦሌ ሜጋ ህንፃ አጠገብ ያለው ሱር ኮንስትራክሽንና መስፍን እንጂነሪንግ፣ በፌዴራልና በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ቀደም ሲል ጀምሮ በርቀት ክትትል- ምርመራ ቀለበት ሥር ከቷቸው እንደነበረ የገለጹልን የኢትዮ-ኦንላይን ምንጮች፣ ለአፈንጋጩ የህወሓት ቡድን የጀርባ አጥንትና ስትራቴጂክ ጉልበት ሆነው ተቀናጅተው እንደሚሰሩ መረጃ አለ ብለዋል፡፡

ሱር ኮንስትራክሽንና መስፍን ኢንጂነሪንግ ጨምሮ ከ80 በላይ የህወሓት (ኢፈርት) ድርጅቶች ከሀገርና ከመንግሥት ጥቅም በተፃረረ ሁኔታ ከአማፂው የህወሓት ቡድን የቀጥታ ትዕዛዝና አመራር እየተቀበሉ የሽብር ስራ ውጥንን ተግባራዊ ለማድረግ በሂደት ላይ እንደነበሩ ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ሁኔታም በአሁኑ ጊዜ ሜጋ ህንፃን ጨምሮ ሱር ኮንስትራክሽንና መስፍን ኢንጂነሪንግ በፌደራል ፖሊስ ከበባ ውስጥና በምርመራ ሂደት ላይ ናቸው::

በሀገሪቱ የፋይናንስና የገንዘብ ዝውውር ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ከጀርባ በህወሓት የሚዘወሩ አንበሳና ወጋገን ባንክ በዕይታ ውስጥ ናቸው ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com