ዜና

‹‹ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን›› በሚል የደም ልገሳ ፕሮግራም ተጀመረ

Views: 278

በጎንደር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የደም ልገሳ ፕሮግራም በከተማ አስተዳደሩ በተዘጋጁ አራት ጣቢያዎች ነው፡፡ መርሃ ግብሩም ለሳምንት የሚቆይ ነው ተብሏል፡፡

ከደም ለጋሾች መካከል አንዱ የሆነው ጌትሽ አቧሆይ እንደገለጸው፣ ለሀገር ደኅንነት ሲባል ዳር ድንበርን እያስከበረ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ልዩ ኃይል ሊደርስ የሚችለውን የደም እጦት ለመተካት ነው ወደ ደም ልግስና የገባነው ብሏል፡፡

ከዚህ የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍል ከሆነም ዝግጁ መሆኑን ወጣቱ ገልጧል፡፡

ወጣት አለማየሁ ታደሰ እንዳለው ደግሞ የዛሬ ደም መለገስ በቀጣይም ማንኛውንም ግዳጅ ለመቀበል ዝግጁነትን ለማሳየት መሆኑን ገልጿል፡፡

እስከ ጥዋት በነበረው ጊዜ በአንድ ጣቢያ ብቻ 39 ዩኒት ደም ተሰብስቧል ሲል የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com