ዜና

‹‹12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ የዲያስፖራ ኢንቨስተሮች የድጋፍ አገልግሎት ተሰጥቷል››

Views: 140

በመጀመሪያ ሩብ ዓመት 12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 336 የዲያስፖራ ኢንቨስተሮች የምልመላና የድጋፍ አገልግሎት መስጠቱን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማውን በቢሾፍቱ ከተማ አድርጓል፡፡

በዚህ ወቅት ለዲያስፖራ ኢንቨስተሮች የምልመላና የድጋፍ አገልግሎት ከመሰጠቱ ባሻገር 825 ዳያስፖራዎች የውጭ ምንዛሪ አካውንት እንዲከፍቱ በማድረግ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

ዲያስፖራውን በማስተባበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ32 ሚሊየን ብር በላይ፣ ለገበታ ለሃገር ከ16 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም ለኮቪድ-19 መከላከያ ከ194 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ መቻሉ ተነግሯል፡፡

በመድረኩ የቀጣይ ሁለት ወራት የስራ ክፍሎች ቼክሊስትና የዲያስፖራ ማህበረሰብ ልማት ሰነድ ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com