ዜና

ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ በአረብኛ ቋንቋ ከሚጽፉ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደረገ

Views: 183

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እና ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳ/ጄኔራል ዛሬ በአረብኛ ቋንቋ በህዳሴው ግድብ ላይ ከሚጽፉ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር እየተደረጉ ባሉ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች አና በቀጣይ መከናወን በላባቸው የትኩረት መስኮች ላይ ውይይት አድርጓል።

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሚዲያ ባለሙያዎች ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ እያደረጉት ያለውን የሚዲያ እንቅስቃሴ በማድነቅ ባለሙያዎችን አመስግነዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎቹ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን አቋም በአረብኛ ቋንቋ ለአረቡ ዓለም የማስተዋወቁ ስራ በስፋት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል።

በቀጣይ ተጨማሪ የትኩረት መስኮችን በመለየት መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግም አምባሳደር ዲና አሳስበዋል።

ከዚህ አንጻር በመካከለኛው ምስራቅና በአረብ አገራት በህዝበ ለህዝብ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝምና መሰል ዘርፎች ላይ በሚዲያና በፐብሊከ ዲፕሎማሲ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አምባሳደር ዲና አንስተዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com