ዜና

በሦስት ከተሞች የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ተመረቁ

Views: 166

በቢሾፍቱ፣ ዱከም እና ሞጆ ከተሞች በ53 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ተመረቁ፡፡

ጣቢያዎቹ ለከተሞቹና አካባቢያቸው እንዲሁም በዙሪያቸው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የኃይል ፍላጎት ምላሽ ለማሟላት የተገነቡ ናቸው ተብሏል፡፡

ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ከፍተኛ የኃይል ጫናና መቆራረጥ ችግሮችን እንደሚቀንሱ ተነግሯል፡፡

ከአዲስ አበባ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት በዱከም ከተማ የተገነባው ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የግንባታ፣ ፍተሻና የሙከራ ሥራው ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁ ነው የተገለጸው፡፡

ከአዲሱ የቢሾፍቱ 400 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ እስከ ዱከም ማከፋፈያ ድረስ 16 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሥመር ዝርጋታ መከናወኑም ተገልጿል፡፡

በሞጆ ከተማ የተገነባው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያም በተመሳሳይ ግንባታ፣ ፍተሻና ሙከራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ነው የተባለው፡፡

የዱከምና የሞጆ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ መሥመርና 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መሥመሮች ያሏቸው ሲሆን፤ ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮችም ተተክለውላቸዋል፡፡

የጣቢያዎቹ ግንባታ በሕንድ፣ በቦስኒያ ሄርዞጎቪኒያና በኢትዮጵያ ሥራ ተቋራጮች እንዲሁም የጀርመንና ስዊዘርላንድ ኩባንያዎች ደግሞ በአማካሪነት ተሳትፈዋል ነው የተባለው፡፡

ግንባታው 85 በመቶ ከፈረንሳይ ልማት ባንክ በተገኘ ብድርና በኢትዮጵያ መንግሥት 15 በመቶ ወጪ መከናወኑን ተዘግቧል፡፡

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com