ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው፡- አንበሳ ባንክ በሕገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር እየታማ ነው፡-

Views: 130
  • ‹‹ኪሳቸውን ለማድረቅ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክን ...ነው!››EthioWikiLeaks)
  • ‹‹በዚህ ዘገባ ላይ ምንም ምላሽ ልንሰጥ አንችልም›› አቶ አቤል ታመነ (የአንበሳ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ማኔጀር)

ኢትዮጵያ የገንዘብ ‹‹ኖት›› ለውጥ ለማድረግ ከተገደደችባቸው ፖለቲካዊ-ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች አንዱና ዋናው ሕገ-ወጥ የገንዘብ ሕትመትና ዝውውር መሆኑ ከሰሞኑ ተገልጿል፡፡ በዚህ የሕገ-ወጥነት ሂደት ውስጥ ደግሞ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በቀጥታ ተሳታፊ ነው በሚል ስሙ እየተነሳና ሠነዶች እየቀረቡበት ነው፡፡

በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በስልክ ያነጋገርናቸው የባንኩ የህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ማኔጀር አቶ አቤል ታመነ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የቀረበውን ዘገባና ማስረጃዎች በዋና ብዙኃን መገናኛዎች ባለመቅረቡ፣ እንደማያስተባብሉ ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጸው፣ በባቲ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የተያዘው ሃያ አራት ሚሊዮን ብር በተመለከተ ግን ቀደም ሲል በባንኩ ድረ-ገጽ ላይ ምላሽ ሰጥተናል ብለዋል፡፡

ኢትዮ-ዊኪሊክስ ዘገባውን ሲጀምር እንዲህ ይላል፡-

“ሕገወጥ እና ሐሰተኛ ገንዘቦችን በሚሰበስቡ ባንኮች ላይ እስከ ኅልውና ማጣት እርምጃ እንደሚወሰድ ጠ/ሚ አብይ አስጠነቀቁ” የሚለውን ዘገባ ስመለከት፣ ወዲያው አዕምሮዬ የመጣው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ነው ይላል ኢትዮ- ዊኪሊክስ።

ምክንያቱን ሲያስረዳም፡- አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ስለመሰማራቱ ተጨባጭ ማስረጃ አለኝ ብሏል። የመጀመሪያው ማስረጃ ከዚህ ቀደም በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተያዘው 22.6 ሚሊዮን ብር ከአንበሳ ባንክ የወጣ መሆኑ ነው ሲል ያስረዳል፡፡

ሁለተኛውና ዋናው ምክንያት ግን አንድ የህወሓት አጭበርባሪ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተሰማራ ባንክ ማቋቋምን አስመልክቶ ለዶ/ርደብረፂዮን እና ለአሉላ ሰለሞን በፃፈው ደብዳቤ ላይ የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጠቀሱ ነው።

ከደብረፂዮን ኢሜይል አፈትልኮ የወጣውን የሰነድ ማስረጃ እና ከዚህ ቀደም ጉዳዩን አስመልክቶ የፃፉኩትን እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ በማለት ሠነዶቹን እንደሚከተለው አስፍሯል።

ሰበር ዜና! ህወሓት አሜሪካ ውስጥ ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪ ድርጅት እንዳለው ታወቀ!

  • አቶ አሉላ ሰለሞን ዋና ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪ ነው!

ከሁለት ሳምንት በፊት ከአንድ የመንግስት ባለስልጣን በደረሰኝ መረጃ መሰረት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የውጪ ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።

ይህን አስመልክቶ ህወሓቶች ወደ ሀገር ቤት የሚላከውን አንድ ዶላር እስከ 40 ብር በሚጠጋ ዋጋ እንደሚገዙ ጠቁመን ነበር ይላል የኢትዮ- ዊኪሊክስ ዘገባ።

ሆኖም ግን፣ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አሜሪካና ካናዳ ከሚገኙ ሰዎች ጋር ባደረኩት ውይይት ከእነዚህ አገራት የሚላከው ገንዘብ ማንነቱ ባልታወቀ አንድ የገንዘብ ላኪ ድርጅት በኩል እንደሚላክ ገልፀውልኝ ነበር ሲል ይገልፃል።

አሜሪካና አውሮፓ ውስጥ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ የሚላክባቸው ትናንሽ ሱቆች በሙሉ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለአንድ ድርጅት እንደሚያስረክቡና ለዚህም አነስተኛ ኮሚሽን እንደሚከፈላቸው ለማወቅ መቻሉን አሳውቋል።

በአሜሪካ የፋይናንስ ህግ መሰረት፣ በዚህ መልኩ የገንዘብ ዝውውር መፈፀም ብዙ አመት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው።

ባለፉት ሁለት ወራት ይህን ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተሰማራውን ድርጅት ስምና አድራሻ ለማወቅ ጥረት አድርጌ አልተሳካልኝም ነበር ብሏል።

ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የኢሜይል አድራሻ አፈትልኮ በወጣው መረጃ መሰረት የተጠቀሰውን ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የሚያከናውነው ድርጅት ተስፋዝጊ አበራ እና አቶ አሉላ ሰለሞን፣ በዶ/ር ደብረፂዮን ዕውቅና የተቋቋመ መሆኑ ተደርሶበታል ብሏል።

ከታች በቀረበው የኢሜይል ማስረጃ መሰረት ባለፈው አመት መጨረሻ አከባቢ አቶ አሉላ ሰለሞን እና ተስፋይዘጊ መቀሌ በሚገኘው ፕላኔት ሆቴል ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተሰማራ ድርጅት ለማቋቋም መስማማታቸው ተገልጿል ሲል ያስረዳል።

ለአቶ አሉላ ሰለሞን በተፃፈው የኢሜይል መልዕክት መሰረት ድርጅቱ ህወሓት እና የኢፈርት ድርጅቶች ያጋጠማቸውን የውጪ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

ድርጅቱም ከ20 በላይ አባላት እንደሚኖሩት፣ በዋናነት ለትግራይ ቀና አመለካከት ያላቸው ወይም የህወሓት አባላት/ደጋፊ መሆን እንዳለባቸው ተጠቅሷል።

ድርጅቱን በማቋቋም ረገድ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አፈትልኮ በወጣው የኢሜይል መልዕክት ውስጥ ተገልጿል። ቀጣይ ስራዎችን ደግሞ በአቶ አሉላ ሰለሞን በኩል እንዲከናወኑ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የዚህን ህገወጥ ድርጅት መቋቋም አስመልክቶ በአቶ ተስፋይዚጊ በኩል እንዲያውቁት መደረጉን ከታች ካለው ኢሜይል መረዳት ይቻላል።

በአጠቃላይ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፂዮን ዕውቅና የተቋቋመው ድርጅት፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ስራ የተሰማራ ሲሆን፣ በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው አቶ አሉላ ሰለሞን ደግሞ ይህን ህገወጥ ተግባር በበላይነት እያስተባበረ ይገኛል ብሏል።

አቶ አሉላ ሰለሞን ቀንደኛ የህወሓት ደጋፊ ሲሆን፣ ከአመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት አሜሪካ ውስጥ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። ህወሓትን በመወከል በአሜሪካ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርግም ይታወቃል ሲል ሃተታውን ያቀርባል።

ከዶ/ር ደብረፂዮን ኢሜይል አፈትለኮ በወጣው መረጃ መሰረት ደግሞ አቶ አሉላ ሰለሞን በአሜሪካ የተቋቋመውን ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪ ድርጅት መስራችና መሪ መሆኑን ለማወቅ መቻሉን ገልጾ፣ ሠነዶቹን በአባሪነት እንደሚከተለው አስፍሯል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com