ቅምሻ ከእኛ- ለእኛ (ኢትዮጵያዬ) የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ተሰናበቱ

Views: 47

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጃን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀበለው አሰናብተዋል።

አቶ ገዱ እንደገለጹት አምባሳደር ታን ጃን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን አገራት ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂያዊ ትብብርና መተማመን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደር ታን ባለፉት 3 ዓመታት በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት በፖለቲካ፣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በህዝብ ለህዝብ እና በቱሪዝም ዘርፎች በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን በማስታወስ ለዚህ ስኬትም የአምባሳደሩ ሚና ከፍተኛ እንደነበር አቶ ገዱ በዚህ ወቅት ገልጸዋል።

አምባሳደር ታን የሸገር ፕሮጀክት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦም አቶ ገዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዚህ ዓመት የተከሰተውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል በተደረገው ርብርብም አምባሳደር ታን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ትብብርና ግንኙነት ከዚህም በላይ የማደግ ሰፊ እድል እንዳለው በመጠቆም አምባሳደሩ ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር አንደሚሰሩ እምነታቸው መሆኑን አቶ ገዱ ገልጸዋል።

አምባሳደር ታን ጃን በበኩላቸው በኢትዮጵያ ቆይታቸው ለስራቸው መሳካት ከመንግስትና ከህዝቡ ለተደረጋላችው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላም የሁለቱን አገራተ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com