ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደረጉ

Views: 59

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከክልል እና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በዋናነት በሀገራዊ መግባባት ላይ የተደረገውን ውይይት ምን እንደሚመስል መገምገም እና ቀጣይ በምን ሁኔታ ውይይቶች ይካሄዱ የሚለውን ለመወያየት ነው።

አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደገለጹት የተደረጉ ውይይቶች በፓርቲዎች መካከል ፉክክር እንዲደረግ በር የከፈተ እና መቀራረብ የፈጠረ ነው ብለዋል።

ታይተው የነበሩ ችግሮች እየተቀረፉ መምጣታቸውንም አንስተዋ፤ በሚቀጥለው ጊዜ ምን ይደረግ በሚለው ጉዳይ ላይም አራት ርእሰ ጉዳዮችን መርጠዋል።
እነዚህም፡- ሕገ መንግስት እና ሕግ መንግስታዊነት ስር በኢትዮጵያ የቅራኔ ምንጭ ላይ ውይይት፣ የፖለቲካ አደረጃጀቶች ምን መምሰል አለበት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሰባሰብ በሚመለከት እና ትክክለኛ ምርጫ ምን ማለት ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲደረጉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫው ስርዓቱ ምን ይሁን እንዲሁም በምን መልኩ ምርጫውን ማከናውን አለበት በሚሉ ጉዳይ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com