የዓለምን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል በዘላቂነት ኢንቨስት ሊደረግ ይገባል ሲል የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

Views: 94

አለም ወደፊት የተሻለ የጤና አገልግሎት እንድታገኝ በጤናው ዘርፍ ዘላቂ ኢንቨስትመንት መደረግ እንዳለበት የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰቡ።

አሁን ካለው እና ከባለፈው ወረርሽኝ ትምህርት ቀስሞ ዝግጅት መደረግ እንዳለበት ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ወረርሽኙን ለመከላከል ኢንቨስትመንት እየፈሰሰ መሆኑን የተገለጹት ዶ/ር ቴድሮስ፤ አስቀድሞ ወረርሽኙን ለመከላከል እየዋለ ያለው ኢንቨስትመንት ዝቅተኛ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በጋራ የምንሰራበት እና ለረጅም ጊዜ የምናቅድበት እንዲሁም በጤናው ዘርፍ ላይ የምናፈሰው መዋእለ ንዋይ ለእርዳታ ሳይሆን የቀጣይ ኢንቨስትመንት አካል መሆን እንዳለበት ዶ/ር ቴድሮስ አሳስበዋል።

እጅ መቀሳሰር የአንድን ሰው ነፍስ አይታደግም ስለሆነም በሕብረት እና በአንድነት ሆነን ይህን አስከፊ ወረርሽኝ በድጋሚ እንዳይከሰት መስራት አለብን ማለታቸውን ሲጂቴኤን ዘግቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com