ስራቸውን በአግባቡ በማያከናውኑ ተቋራጮችና አማካሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አቶ ሽመልስ ገለጹ

Views: 51

ስራቸውን በአግባቡ በማያከናውኑ የስራ የቋራጮች እና አማካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልፀዋል።

የ2012 በጀት ዓመት የኦሮሚያ ክልል የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና በክልሉ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የተሰማሩ የስራ የቋራጮች እና አማካሪዎች ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት አቶ ሽመልስ በክልሉ ፕሮጀክቶችን በመፈፀም ረገድ ችግሮች የነበሩ መሆኑን አንስተው፣ በ2012 በጀት ዓመት ግን “ የመጨረስ ዘመን” በሚል ክልሉ ለዘርፉ በሰጠዉ ከፍተኛ ትኩረትና በተደረገዉ የተቀናጀ ክትትል ከ4 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን እንደገለፁ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com