ቅምሻ ከወዲህ ማዶ፡- ደቡብ ሱዳን ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ልትከፍት ነው

Views: 39

በደቡብ ሱዳን በኮቪድ 19 ምክንያት ለስድስት ወራት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎችን ከዛሬ ጀምሮ ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር እንደሚጀመሩ ተገለፀ፡፡

ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም እንዲከፈቱ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሳልቫኬር መሪነት ካቢኔው ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሯ ኤልዛቤት አችዩ ዮል እንዳሉት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ በማሳየቱ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲከፈቱ ሆኗል ብለዋል፡፡

መንግስት በመጋቢት ወር የመጀመርያ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ሲያገኝ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ዘገባው አስታውሷል፡፡

የአገሪቷ የጤና ሚኒስትር በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በሰጡት መግለጫ ትምህርት ቤቶች ዳግም መከፈታቸው መልካም መሆኑን ጠቅሰው፤ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የመማርያ ክላሶች በማዘጋጀት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com