ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለችግር የተጋለጡ 155 ሺህ ሰዎችን ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ ነው

Views: 34

በተለያዩ ምክንያች ለችግር የተጋለጡ 155 ሺህ ሰዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ተሲሳ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ ገጠር እና ከተማ የሚኖሩት ሰዎች ለችግር የተጋለጡት ባለፈው ዓመት ተፈጥሮ በነበረ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።

ለጉዳት ካጋለጧቸው ምክንያቶች መካከል ግጭት፣ ጎርፍና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ይገኙበታል።

ለነዚህ ወገኖች የምግብ፣ አልባሳት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ የመኖሪያ ቤት ጥገና፣ የእርሻ መሣሪያ እና ምርጥ ዘር እንዲሁም የመጠጥ ውሃ በማመቻቸት ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን አስረድተዋል።

ለመልሶ ማቋቋሙ ስራ ከመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መሆኑን ጠቅሰው የፌደራል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

በ2013 ዓ.ም. የተጎጂዎችን ቁጥር በመቀነስ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እቅድ መዘጋጀቱንም አቶ ታረቀኝ አስረድተዋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com