ዑጋንዳና ታንዛኒያ በ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ማስተላለፊያ መሥመር ለመዘርጋት ተስማሙ

Views: 41

ዑጋንዳና ታንዛኒያ 1ሺህ 445 ኪ.ሜ የድፍድፍ ነዳጅ ቧንቧ መሥመር ለመገንባት የሚያስችለውን ሥምምነት ተፈራረሙ።
የ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት የዑጋንዳ የነዳጅ ቦታዎችን ከታንዛኒያ ወደብ ታንጋ ወደብ ጋር እንደሚያገናኝ የቢቢሲ ዘገባ አስታውቋል።
ዘገባው አያይዞም በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የሁለቱም አገሮች ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል ብሏል።
በ2006 በዑጋንዳ የነዳጅ ክምችት የተገኘ ቢሆንም የኤክስፖርት ቧንቧን ጨምሮ በመሠረተ ልማት እጥረት በከፊል ምርቱ ዘግይቷል።
በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ዋና የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ለመሆን የተዘጋጀው ግንባታው የሚጀመርበት ቀን ገና አልተገለጸም።
ዕቅዱን የቻይና ብሔራዊ የባህር ዳርቻ ነዳጅ ኮርፖሬሽንና ከዑጋንዳ እና ታንዛኒያ መንግሥታት ጋር በመሆን የፈረንሳዩ ግዙፍ ነዳጅ ኩባንያ ቶታል ዕቅዶችን እየመራ መሆኑን ዘገባው አስታውቋል።
ወደ 80 ከመቶ የሚሆነው የነዳጅ መሥመር ዝርጋታ በታንዛኒያ ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን ፕሮጀክቱ ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ታንዛኒያዉያን የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የመንግሥት ቃል አቀባይ ሀሰን አባሲን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com