ኢትዮጵያ ነባሮቹን በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም ልትጀምር ነው

Views: 24
ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ነባሮቹን ከመተካት ባሻገርም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል ነው ያሉት።
እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ እንደሚረዱም ጠቅሰዋል።
በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ያግዛሉ ብለዋል።
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com