ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ

Views: 58

በአዲስ አበባ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።
በእለቱ በደረሰው የእሳት አደጋ በበርካታ የንግድ ሱቆች፣ መጋዘኖች እና ሬስቶራንቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች ዛሬ የ6 ነጥብ 5 ብር በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አድርጓል።

በተጨማሪም የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 600 ሺህ ብር እና ለአዲስ አመት በዓል ሁለት በሬዎችን በስጦታ አበርክቷል።

የገንዘብ ድጋፉንም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ለተጎጂዎቹ ማስረከባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com