‹‹ከተሞችን በማስዋብ ሰፊ ጠቀሜታን ለማግኘት የታቀዱት ፕሮጀክቶች ታላቅ ሃሳብ ናቸው››

Views: 40

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የታቀዱት ከተሞችን የማስዋብ ፕሮጀክቶች ሰፊ ጠቀሜታን የያዙና ታላቅ አሳብ ናቸው ሲሉ የቻይና መንግሥት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አማካሪ ሊው ዩ ገለጹ፡፡ ለፕሮጀክቱ መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የውጭ ሀገር ተወካዮች፣ የሀገር ውስጥ ግለሰቦችና ተቋማት በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ላይ በማማከርና በተለያዩ አግልግሎቶች ከተሳተፉት ባለሙያዎች መካከል ሊው ዩ እንዳሉት በዚህ ታላቅ እና ታሪካዊ ፕሮጀክት ላይ ተሳትፌ አሻራዬን በማኖሬ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡

“አዲስ አበባ ማለት አዲስ ህጽዋት ማለት ነው፤ ይህም ፕሮጀክት ይህን ስያሜ ይዞ የሚጓዝ ነው” ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አካባቢን ከማስዋብ ባለፈ ሰፊ ጠቀሜታ አለው፤ ከዚህ በኋላም የሚከናወኑት ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸው አልጠራጠርም ብለዋል፡፡

“ዛሬ ታላቅ ቀን ነው፣ ታሪካዊ ቀንም ነው፣ በዚህ ስራ ላይ ለተሳተፉት በተለይም ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋልሁ” ነው ያሉት አማካሪዋ፡፡

“ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት ቻይናን እንደምወደው ኢትዮጵያንም እንደ እናት አገሬ እወዳታሉ” ያሉት ሊው ዩ ኢትዮጵያና ቻይና እስከዛሬው የነበራቸው ግንኙነትም በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹ጊዜ ይሄዳል አዲስ አመትም መጥቷል ለመላው ኢትዮጵያዊንም መልካም አዲስ አመት እመኛለሁ›› ብለዋል፡፡

የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት አዲስ አበባን ለኑሮ የምትመችና ተመራጭ ከተማ እንድትሆን እንደሚያደርጋት የገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ሚስተር ታን ጂያን ናቸው።

ፓርኩ የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴቶችን በውስጡ ከመያዝ ባለፈ ጥንታዊ ገናናነትን ጭምር የሚያንጸባርቅ መሆኑን ነው የገለጹት።

ይህም ኢትዮጵያን በአለም ደረጃ ለጉብኝት ከሚመረጡ ሀገራት መካከል አንዷ ያደርጋታል ያሉት አምባሳደሩ፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ከሀገር አልፎ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ የሚያደርጋት ፓርክ ጭምር ነው ሲሉም አክለዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com