ሀገር ለመገንባት ጥሪ ቀረበ

Views: 38
  • ለ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክት የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ለ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ። ባንኩ የገበታ ለአገር ፕሮጀክትን አስመልክቶ ከፋይናንስ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ትናንት ውይይት አድርጓል።

ፕሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 10 ቀን 2012 ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ፕሮጀክቱ በጎርጎራ፣ በወንጪና ኮይሻ እንደሚለሙም ተገልጿል። በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለፕሮጀክቱ 30 ሚሊዮን ብር ለመስጠት በቦርዱ አማካኝነት መወሰኑን ገልጿል።

ሌሎች የውይይቱ ተሳታፊዎች ፕሮጀክቱን በፋይናንስ በሚደግፉበት ሁኔታና የፕሮጀክቱ የፋይናንስ አጠቃቀምና ግልጽነት ዙሪያ ሀሳብና ጥያቄ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ፕሮጀክቱ በግልጽ የፋይናንስ ሥርዓት የሚመራ መሆኑን ገልጸዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com