ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) ትምህርት ቤቶች ማስተማር ሊጀምሩ ነው

Views: 51

የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል ለማስተማር እየተዘጋጁ መሆቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ገለጹ፡፡ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የኮሮናን ቫይረስ ስርጭት በመከላከል የሚሰጠውን ትምህርት እውን ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የአዲስ አበባ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች አስታወቁ፡፡

ተቋማቱ በትምህርት ዘመኑ ተማሪዎችን ለመቀበል በሚያደርጉት ዝግጅት ተማሪዎች ጤናቸው ተጠብቆ እውቀት የሚገበዩበትን ስርዓት ለመተግበር የተደረገውን ጥረት ኢዜአ በትምህርት ቤቶቹ ተዘዋውሮ ቃኝቷል፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚያስችል መንገድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንዳሉ የገለጹልን የሬኔሳንስ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ነዋይ ጌታቸው ናቸው፡፡

የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ንጽህናን መጠበቅ የሚያስችሉ የውሀ ሮቶዎች የማዘጋጀት፣ የመመገቢያ ቦታዎች እድሳት እና መጸዳጃ ቤቶችን ንጹኅና ለማስጠበቅ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የእውቀቴ ወገኔ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርእሰ መምህር አቶ በሱፍቃድ ዓለሙ በበኩላቸው ተማሪዎችን ከመመዝገብ ባለፈ ኮሮናን በመከላከል ትምህርት ለማስጀመር የመንግስት መመሪያን እየጠበቁ ናቸው::

በኮሮና ምክንያት በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ነባር ተማሪዎች ተመዝግበው ክፍት ቦታ ካለ ብቻ አዲስ ተማሪዎች እንቀበላለን ያሉት ምክትል ርእሰ መምህሩ፣ በተቻለ መጠን ቫይረሱን ለመከላከል በሚያስችል ደረጃ የመማሪያ ቦታዎች ምቹ ለማድረግ ትምህርት ቢሮ በሚያወጣው መስፈርት እንደሚሰሩም ጠቁመዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com