ቅምሻ ከኛው- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) በትግራይ መራጮች ድምጽ በመስጠት ላይ ናቸው

Views: 46

የትግራይ ክልል እያካሄደ በሚገኘው ክልላዊ ምርጫ ዛሬ ከንጋት ጀምሮ መራጮች ድምጽ መስጠት ጀምረዋል። መራጮች ከንጋት 12፡00 ጀምሮ በ2 ሺህ 672 የምርጫ ጣቢያዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ በነሐሴ መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ሀገር አቀፍ ምርጫ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ፤ በትግራይ በተናጠል እየተካሄደ የሚገኘው ክልላዊ ምርጫ ሕገ-ወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት የፌደሬሽን ምክር ቤት መወሰኑ ይታወሳል።

መቀለ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ከንጋት 10፡30 ጀምሮ ምርጫ ጣቢያዎች ፊት ለፊት ተሰልፈው መመልከቱን ገልፆልናል።

በክልላዊ ምርጫው ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በክልሉ 38 የምርጫ ክልሎች እንዳሉ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን መግለጹ ይታወሳል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com