ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) ትምህርት ቤት እንደ ሕክምና ማዕከል

Views: 43

ተማሪዎች ከሚደረስባቸው የስነ ልቦና ጉዳት እንዲላቀቁ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክረ ሃሳብ ቀረበ፡፡ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤት በመዘጋቱ ቤታቸው የዋሉ ተማሪዎች ለተለያዩ ጉዳቶች እየተጋለጡ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ተማሪዎች ያለ እድሜ ጋብቻ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ጉልበት ብዝበዛና ይህንን ተከትሎ በሚመጣ የስነ ልቦና ችግር እየተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች አሳይተዋል።

እነዚህን ችግሮች ለማስወገድና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ የትምህርት ሚኒስቴር ኮሮናን በመከላከል ትምህርት መጀመር የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች እያጠና ይገኛል ተብሏል።

በተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ተማሪዎች የትምህርት መጀመርን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ወላጆች የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ልጆቻቸው ትምህርት ቤት ሲሄዱ ለኮሮና ቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚለው ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

እነዚህን ተቃራኒ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት ትምህርት ሚኒስቴር እንደ አካባቢዎቹ ወቅታዊ የኮሮና ስርጭት ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ መክፈት የሚያስችሉ መንገዶችን እየገመገመ ይገኛል ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው ጥናት ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት በአንድ ክፍል ውስጥ ከ 20 እስከ 25 ተማሪዎችን ማስተማር፣ የንፅህና መጠበቂያ ለትምህርት ቤቶች ማቅረብ፣ ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት የሚሉ አማራጮች ቀርበዋል።

ጥናቱ ሲጠናቀቅ በሚቀርበው ተጨማሪ ምክረ ሃሳብ መሰረት አስፈላጊው ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ትምህርት ለመጀመር ጥረት እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚድያ ገፅ ያገኘነው ያሳያል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com