ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) ቀዳማዊት እመቤት ማዕድ አጋሩ

Views: 47

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት 100 ለሚሆኑ ችግረኛ አይነስውራን ማእድ አጋሩ።

በዛሬው እለት በተከናወነው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ሩዝ፣ ዘይት እና ዱቄት አበርክተዋል።

የቀዳማዊ እመቤት ጽሕፈት ቤት ችግረኛ አረጋዊያንን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሌሎችንም ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል።

ጽሕፈት ቤቱ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን በማሰራት የድርሻውን በመወጣት ላይም ይገኛል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com