ቅምሻ ከእኛ- ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) ውጭ ጉዳይ አዲስ መርሃ-ግብር አወጣ

Views: 58

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ፈላጊዎች አዲስ መርሃ ግብር አውጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። በኮሮና ቫይረስ መከሰት ሳቢያ ሰነዶች እንዲረጋገጡላቸው ወደ ሚኒስቴሩ የሚመጡ ተገልጋዮች ወረፋ እና መጨናነቅ ሲያጋጥማቸው ነበር።

ችግሩ የተከሰተው ሰራተኞች ለቫይረሱ ተጋላጭ አንዳይሆኑ በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ በመደረጉና አገልግሎት ፈላጊዎችም በቤታቸው ሆነው በስልክ ምዝገባ እንዲያካሄዱ በመደረጉ ነው።

ሆኖም፣ አሰራሩ ውጤታማ ባለመሆኑ ወረፋ እና መጨናነቅ ሲፈጥር መቆየቱን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ዮሃንስ ሾዴ ገልጸዋል።

የተፈጠረውን ክፍተት በመረዳት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ማሻሻያና አዲስ መርሃ ግብር ወጥቶ ተገልጋዮች በአግባቡ እየተስተናገዱ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህም በመሆኑ በተገልጋዮች ላይ ሲፈጠር የነበረው ወረፋና መጨናነቅ አሁን ላይ ተቃሏል ብለዋል።

አዲስ ከወጣው መረሃ-ግብር ውጭ አገልገሎት ለማግኘት የሚመጡ እንዳሉ የገለጹት ዳይሬክተር ጄኔራሉ፣ ከእለቱ ባለ ተራ ተስተናጋጆች የሚተርፍ ጊዜ ካለ አገልገሎት ያገኛሉ ብለዋል።

በእለቱ ሲስተናገዱ ከነበሩ ተገልጋዮች መካከል ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡት ወይዘሮ ሰላም አበራ እንዳሉት ለባለጉዳዮች ፕሮግራም ወጥቶ መስተናገዳቸው የነበረውን ወረፋ እና አንግልት አስቀርቷል።

አዲሱ አገልግሎት አሰጣጥ ስራን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ ለኮሮናቫይረስ መጋለጥ እንዳይኖር መጨናነቅን ያስቀረ መሆኑንም ገልጸዋል።

ሌላኛዋ በለጉዳይ ወይዘሮ ሲቲ አህመድ በበኩላቸው ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ለብዙ ቀናት መጉላላታቸውን ገልጸው አሁን ላይ ግን በፍጥነትና በአጭር ጊዜ አገልገሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com