ቅምሻ – ከእኛ ለእኛው (ኢትዮጵያዬ) #  “ልትገድሉኝ እንደምትፈልጉ አውቃለሁ” ጠቅላይ ሚንስቴር ዓብይ አህመድ

Views: 262

ከላይ የተጠቀሰውን ሃሳብ ጠቅላይ ሚንስቴሩ የተናገሩት፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ሲሆን፣ የኦነግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አራርሳ ላቀረቡላቸው ጥይቄዎች መልስ ይሰጡ በነበረበት ወቅት ነበር፡፡ በተጨማሪ፣ ኦነግ እግሩን ሁለት ቦታ ተክሎ እንደሚንቀሳቀስ፣ ማለትም በሰላማዊና በትጥቃዊ ትግል ውስጥ መሰማራቱን እንደደረሱበትና ጉዳዩን የሚያውቁ መሆናቸውን በተዘዋዋሪ መንገድ ለመግለጽ ፈልገው ይመስላል፡፡ በንግግራቸው ላይ አክለውም፣ አንዱን ብትመርጡ ይሻላችኋል በማለት ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ ለማስተላለፍ ሞክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስቴሩ ስም ጠርተው ባይናገሩም፣ በሰላማዊ ትግል ተሰማርቼአለሁ የሚለው ኦነግንና ትጥቃዊ ትግልና የሽብር ጥቃት በማካሄድ ላይ የሚገኘው ኦነግ ሸኔን ለመጠቆም ፈልገው ነው፡፡ እንደሚታወቀው፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት ከ150 በላይ የሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ በተካሄደው ግድያም ሆነ ንብረት በማውደሙ ሂደት ዋነኛ ተሳታፊው ኦነግ ሸኔ ሲሆን፣ የኦነግ አመራር በዚህ ድርጊት እጁ አልነበረበትም ብሎ መናገር ይቻል ይሆን?

ኢትዮኦንላይን

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com