ዜና

የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውኃ ሚኒስትሮች ማምሻውን ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል

Views: 360

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውኃ ሚኒስትሮች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌት ላይ የቪዲዮ ውይይት ዛሬ ማምሻውን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በባለሙያዎቻቸውና በውኃ ሚኒስትሮቻቸው አማካኝነት ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲያካሂዱ እንደነበር ይታወሳል።

ይሁንና በተለይ ግብጽ በውይይቱ ጊዜ አቋሟን በመቀያየርና አዳዲስ ሀሳቦችን በማምጣት ውይይቱ እንዲራዘም ከማድረግ ባለፈ ያለውጤት እንዲጠናቀቅና ስታደርግ ቆይታለች።

ግብጽ በግድቡ ውኃ አሞላል ላይ ይዛ በቀረበችው አዲስ ዕቅድ ምክንያት ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ሦስቱ አገራት ለአንድ ዓመት ያህል ምንም አይነት ውይይት ሳያደርጉ ቆይተዋል።

በዚህ መሐል በአሜሪካና ዓለም ባንክ ታዛቢነት አገራቱ በግድቡ ውኃ ሙሌት ላይ ውይይታቸውን በድጋሚ በዋሽንግተን መጀመራቸው ይታወሳል።

ይሁንና፣ የአሜሪካ መንግስት ቀደሞ በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት መግባቱን በመቃወም ኢትዮጵያ በውይይቱ ራሷን አግልላለች።

ምንም እንኳን የሦስቱ አገራት ውይይት መቋጫ ባያገኝም፣ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በማፋጠን ከመጪው ሐምሌ ወር ጀምሮ የተወሰነ ውኃ ለመያዝ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

የሦስቱ አገራት የውኃ ሚኒስትሮች ዛሬ አመሻሽ ላይ የግድቡ ውኃ ሙሌትን አስመልክተው በቪዲዮ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com