የግመል ወተት እና የጤና በረከቱ

Views: 258

መነሻ

በአገራችን ከላም-ወተት ቀጥሎ፣ ከፍተኛ የወተት ምርት የሚገኘው ከግመል ነው፡፡ በአርብቶ አደሮች አካባቢ እንደ ዋቢ ምግብ፣ በደንብ ጠቀሜታ ላይ ውሏል፡፡ በእስያ እና በሰሜን አፍሪካ አገራት ለብዙ ሺህ አመታት ሲጠቀሙት ኖረዋል፡፡ ከምግብነቱም ሌላ፣ ከፍተኛ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በብዙ ጥናት ተረጋግጧል፡፡

ስለሆነም፣ በሌሎች አገራት ለብዙ በሽታ “የግመል ወተት ጠጡ” ተብሎ ይታዘዛል፡፡ ሆኖም፣ በብዙ የኢትዮጵያ ከተሞች እና ደገኞች ዘንድ ወተቱ እውቅና የለውም፡፡  በ2ዐዐ8 እ.ኤ.አ የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት “በዓለም ላይ 2ዐ ሚሊዮን ግመሎች ይገኛሉ፤ ከነዚህም ውስጥ 2.4 ሚሊዮን በኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው፡፡

ይህም፣ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል” ብሎ ነበር፡፡ እነዚህም በአገሪቱ ምሥራቅ ክፍሎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት ባለባቸው የአፋር ክልል እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በይበልጥ ደግሞ፣ የእነ በድሉ ደምሴ ጥናትን  በሚከተለው ሊንክ ላይ አንብቡ፡-

https://academicjournals.org/journal/AJMM/article-full-text-pdf/1804DD265491

Production and marketing of camel milk in Eastern Ethiopia

 1. የግመል ወተት ምን ምን ይዟል፤

ልክ እንደ ላም ወተት ካሎሪ፣ ፕሮቲን፣ እና ካርቦን ይዟል፡፡ መጠነኛ ቫይታሚን ቢ፤ ካልስየም  እና ፖታስየም አለው፡፡

ከፍተኛ መጠን ሞኖ አንሳቹሬትድ እና ፖሊ አንሳቹሬትድ ፍቲ አሲድ፣ አልቡሚን፣ ላክቶፈሪን፣ግሎቡሊን፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኢ፣ ማንጋኒዝ፣ ብረት፣ ሆርሞን ኢንሱሊን የተባሉ ንጥረ ምግቦችን እና ሌሎችም ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡

(camel milk has very high concentration of mono-and polyunsaturated fatty acids, serum albumin, lactoferrin, immunoglobulin’s, vitamins C, and E, lysozyme, manganese and iron, as well as the hormone insulin) https://www.ejfa.me/index.php/journal/article/view/1024

Emirates journal of Food and Agriculture

 1. የግመል ወተት የጤና ጠቀሜታ

በዋናነት የተረጋገጠ ፈውስ የሚሰጠው፡-

 • ለሆድ እና የአንጀት ውስጥ ህመም፤ stomach and intestinal disorders,
 • ለስኳር በሽታ ዓይነት አንድ፤    Diabetes-1
 • ለምግብ አለርጂ፤    food allergy

ስቀጥል፣

 • የደም ኮልስትሮልን ለመቀነስ፤ reduce cholesterol levels in the blood
 • የደም ዝውውር ለማስተካከል፣
 • ለልብ ጤንነት፣
 • ለዕድገት እና ጥንካሬ፣
 • ለእርጉዝ እናቶች፤
 • ፓስሪዮሲስ የተባለ በሽታን ለማስወገድ፣ to avoid psoriasis disease,

(ይህ በሽታ እንደ ፎረፎር ሆኖ ቆዳን የሚያበላሽ፣ በቀላል የማይዳን አዛ የሆነ የቆዳ በሽታ ነው፡፡)

 • በሰውነት ውስጥ የሚከሰት ብግነትን ለማዳን፣ to heal inflammation in the body
 • የቲቢ ታማሚን ለመርዳት፤    assist patients with tuberculosis,
 • የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓት ለማጎልበት፣ helping to strengthen the human immune system,
 • የነቀርሳ ሴሎችን እድገት ለመቀነስ፣, to reduce growth the cancer cells  እና
 • ኦቲዝምን ለመፈወስ cure autism.

ይረዳል የግመል ወተት፡፡

 1. አጠቃቀሙ

በጥሬው፣ በትኩሱ እና በንጽህና የታለበ መሆን አለበት፡፡ ለምግብ ሲፈለግ ሊፈላ ይችላል፡፡ ነገር ግን ተፈልቶ ለመድኃኒትነት አይሆንም፡፡ በሽታ ተዋጊ የሆነው ንጥረ ነገር ሲፈላ ሊጠፋ ይችላል፡፡

 1. የአጠቃቀም ጥንቃቄ

ጠጥቶ የማያውቅ ሰው ለመጀመሪያ ቀናት ወይም ሳምንታት ሲጠጣው፣ አንዳንድ ክስተት ሊኖር ይችላል፡፡ ለምሳሌ ተቅማጥ፣ የሆድ ህመም ወይም ሌላም ክስተት፡፡

ስለዚህ፣ ቀስ እያሉ እየተለማመዱ መጠጣት ነው፡፡ “የግመል ወተትን ለፈውስ እፈልጋለሁ!” ያለ ሰው፣ የግመል አርቢዎች ወደሚኖሩበት ሄዶ ለጊዜው አብሮ እየኖረ፤ የግመሏን ጤና እየተንከባከበ፤ የጤነኛ ግመል ወተቱን እየጠጣ ፈውሱን ቢሻ ይበጀዋል፡፡

አለዚያም፣ ከወተት አምራቹ በነጋዴዎች ተገዝቶ ሲቀባበሉት ከተማ ያደረሱትን መተማመን ያስቸግራል፡፡

ወደፊት የግመል ወተት አቀናባሪ አምራች ሲገኝ ያኔ “እሰየው” ይሆናል፡፡ ያኔ በማቀዝቀዣ ውስጥም ማቆየት ይቻላል፡፡

ማጠቃለያ

እንደ ላም ወተት የግመል ወተት አቀናብረው በጥራት የሚያቀርቡ ድርጅቶች መበረታታት አለባቸው፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ የእኛ ሰው ለብዙ በሽታ በብዙ ሐኪም ቤት ሲንከራተት ከሚቆይ፤ለምንስ “የግመል ወተት ፈውስ ነው” ለተባሉት ሕመሞች፤ የግመል ወተት ከሚገኝበት ሄዶ አይጠጣም?!

በ2ዐ11 ዓ.ም ኢትዮፓናራማ ቢቢሲ/ አማርኛን ጠቅሶ ባለጊዜው የግመል ወተት በሚል ርዕስ ሥር

“ዓለም ላይ ቀዳሚ የግመል ወተት አምራቾች የምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ናቸው። የአውስትራሊያ መንግሥት በቀጣይ አምስት ዓመታት የግመል ወተት ንግድን እንደሚያሳድግ ይናገራል።” ብሎ ነበር፡፡ http://www.ethiopanorama.com/?p=106562&lang=en

አቤቱ የእኛ መንግሥት መቼ ይሆን የግመል ወተትን ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ገበያ ወደ ከፍተኛ ንግድ የሚያስገባው?! ይህ የእኛ ጥያቄ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com