አጫጭር ዜና
አጫጭር ዜና

የኢዜማ የፓርላማ አባላት ጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቁ

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ600 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ!

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ጀመረ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ 24 ተቋማት መገኘታቸውን አስታወቀ

“መንግስት ለሚረግፉ ዜጎቻችን ህይወት ተጠያቂ ነው” ኢዜማ

በመዲናዋ 3ኛው ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአምባሳደር ቲቦር ናዥ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገቡ

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርኩ የመከላከያ ሚኒስትር ሁሉሲ አካር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ በዓለ ሲመት ሞቃዲሾ ገቡ

በአፍሪካ ቀንድ የሕብረቱ ከፍተኛ ተወካይ እንዲሁም የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ

የሰኔ ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

ካርድ “የዘፈቀደ” ያለውን የጋዜጠኞች እስር በመቃወም የሕግ የበላይነት ይከበር ሲል ጠየቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ናይጄሪያ ገቡ

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ ሥልጣን ተረከቡ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፤ መንግሥት ለሕዝብ ደህንነትና ሰላም ቅድሚያ በመስጠት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቀ

ገዢው ፓርቲ አባል የሆነበት ምክር ቤቱ መንግስት ግዴታውን ባለመወጣቱ ችግሮች መባባሳቸውንም ገልጿል ም/ቤቱ፤ መንግስት “የደህንነት ስጋት አለብን” ላሉ ዜጎች ፈጣን ምላሽ መስጠት ነበረበት ብሏል ገዢው ፓርቲ አባል የሆነበት የፖለቲካ ፓርቲዎች…

በጊምቢው ጥቃት በተገደለችው እናቷ እቅፍ የተገኘችው የ15 ቀኗ ጨቅላ ሕጻን

አይሻ ሰይድ የተወለደችው በደቡብ ወሎ ዞን፣ አርጎባ ወረዳ ውስጥ ነው። እዚያ ትወለድ እንጂ እድገቷ ግን በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ ፣ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ነው። ወደዚያ ያቀናችው በ1990 ዓ.ም ነበር። ያኔ…

ሱዳን የኢትዮጵያ ሠራዊት ወታደሮቼን ገደለ ስትል ከሰሰች

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ምርኮኛ የነበሩ ሰባት የሱዳን ወታደሮችን እና አንድ ሲቪል ገድሏል ስትል ሱዳን ከሰሰች። የሱዳን መንግሥት በመገናኛ ብዙኃን ገጹ እንዳሰፈረው፣ አንድ ሲቪልን ጨምሮ ሰባት ወታደሮቹ በኢትዮጵያ መከላከያ ተገድለዋል። ትላንት…

አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን አጠናቆ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መሸጋገሩን ገለፀ

አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአራት ምዕራፎች የተከፈሉ ተግባራት እንዳሉትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን አጠናቆ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መሸጋገሩን የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ…

መንግስት በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች ”የጅምላ ግድያ” የፈፀሙት ለፍርድ እንዲያቀርብ የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ ይህን የጠየቀው ”በንፁሃን ዜጎች ላይ በአሸባሪዎች እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ አጥበቀን እናወግዛለን!” ሲል ሰይሞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣውና ለአሻም በላከው መግለጫ ላይ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች…

አብን አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎን ወቀሰ

አብን አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎን ወቀሰ ~ የዘር ተኮር ጭፍጨፋው በአጀንዳነት ተይዞ ለውይይት እንዲቀርብ ጠየቀ፣ ~ ጠ/ሚ ዐብይም ስለጉዳዩ ፓርላማ ቀርበው እንዲያስረዱ ጠይቋል፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ…

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ያሰለጠናቸውን አብራሪዎች እያስመረቀ ነው

‘’ነብሮች 2014’’ በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር ሀይል በበረራ ሙያ ያሰለጠናቸውን አብራሪዎች እያስመረቀ ነው። በምረቃ መርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ…

በምዕራብ ወለጋው ጥቃት ወቅት ታግተው የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ ተገለጸ

በምዕራብ ወለጋው ጥቃት ወቅት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች በታጣቂዎቹ ታግተው መወሰዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን አመለከተ። ኮሚሽኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት አስመልከቶ ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በርካታ ሰዎች…

ወደ ትግራይ ክልል በሚጓጓዙ ነገሮች ላይ የተጣሉ ጥብቅ ፍተሻዎች እንዲላሉ የአውሮፓ ህብረት ጠየቀ

የአውሮፓ ህብረት ለትግራይ አድልቷል በሚል የሚነሱ ጥያቄዎችንም አስተባብሏል ትግራይ ክልል ባንክ እና ቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ህብረቱ አሳስቧል ወደ ትግራይ ክልል በሚጓጓዙ ነገሮች ላይ የተጣሉ ጥብቅ ፍተሻዎች እንዲላሉ የአውሮፓ…

ባንኩ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን ገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ። የባንኩ የከረንሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው…

ቻይና በፈረንጆቹ 2028 የመጀመሪያውን የጠፈር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ልትገነባ ነው

ቻይና በፈረንጆቹ 2028 የመጀመሪያውን የጠፈር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ማቀዷን አስታወቀች። የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢውን በህዋ ላይ ለመገንባት የሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሷን የቻይና የሕዋ አካዳሚ ቴክኖሎጅ አስታውቋል። በሕዋ ላይ…

በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ተጨማሪ ኃይል ካልተሰማራ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም ይችላል – ኢሰመጉ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዥንጋ ወረዳ ተጨማሪ ኃይል ካልተሰማራ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ሰኔ…

ጠ/ሚ ዐቢይ “የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት አንታገስም” አሉ

ጠ/ሚ ዐቢይ “በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት ተቀባይነት የለውም” ብለዋል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮና የኦሮሚያ ክልል አስታውቀዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “የሰው…

የስፖርት ውርርድ ወይም ቤቲንግ እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገለፀ

የስፖርት ውርርድ ወይም ቤቲንግ እንዲታገድ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቀ። በሚኒስቴሩ የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አበበ ሃይማኖት እንደተናገሩት÷ ከታዳጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም…

ብሪታንያ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች

ከአሁን ቀደም በሩሲያ ቱጃሮች ላይ ማዕቀቦችን መጣሏ ይታወሳል ማዕቀቡ የፕሬዝዳንት ፑቲን ደጋፊ ናቸው በሚል የተጣለ ነው ብሪታንያ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ክሪል ላይ ማዕቀብ ጣለች፡፡ ማዕቀቡ ፓትርያርክ ክሪል የሩሲያ ጦር በፕሬዝዳንት…

ተመድ ስለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያወጣውን ሪፖርት ኤርትራ አልቀበለውም አለች

ተመድ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት “በኤርትራ ያለው የስበዓዊ መብቶች ጥሰት ሁኔታ እየተባባሰ ነው” ማለቱ ይታወሳል ኤርትራ “በሰብዓዊ መብቶች በኩል ያሉት ጉድለቶች”ን ለማሻሻል እየሰራሁ ነው ብላለች ኤርትራ በሀገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን…

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሀይል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሰማራ ፕሬዚዳንት ኬንያታ ጠየቁ

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሀይል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሰማራ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጠይቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ያለበትን የፀጥታ ችግር ወደ ነበረበት ለመመለስ በማሰብ ነው የቀጠናው ተጠባባቂ ሀይል…

1ሺ 128 ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀለ ቀልጠው ቀሩ

«ለሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ከተጓዙት ሦስት ሺህ 297 ተሽከርካሪዎች አንድ ሺህ 128ቱ አልተመለሱም» ሰብዓዊ ድጋፍ ጭነው ወደ ትግራይ ከተጓዙት ሦስት ሺህ 297 ተሽከርካሪዎች ውስጥ አንድ ሺህ 128ቱ እንዳልተመለሱ የኢትዮጵያ አደጋ…

የትምህርት ሥርዓቱን የጥራት ችግር ለመፍታት የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ ሰኔ 8/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ የሚስተዋለውን የጥራት ችግር ለመፍታት የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ። የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ ከተመደቡት የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ በዘርፉ የአምስት አመት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ማረጋገጥ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል። ለዚህ መሳካት አጠቃላይ የማኅበረሰቡና የትምህርት ተቋማት ድርሻ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው አዲስ የተመደቡት የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮችም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የቦርድ አመራሮቹ በበኩላቸው በሚኒስቴሩ የተጀመረው የሪፎርም ሥራ እንዲሳካ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይም የሙስና እና ብልሹ አሰራሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ጠቅሰው ችግሩን ለመፍታት የጋራ ጥረት ይጠይቀናል ብለዋል። የትምህርት ተቋማት የእውቀት ማእከላት እንጂ የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያዎች መሆን ስለሌለባቸው ለዚህም በልዩ ትኩረት መስራትን ይጠይቀናል ነው ያሉት። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ የሆኑ ብቁ እና በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ምሁራን መፍለቂያዎች ሊሆኑ ይገባል ብለዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የሥራ አመራር የቦርድ አባላት መመደባቸው ለተጀመረው ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር የተደረገው የውይይት መድረክም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተጀመረውን የሪፎርም ሥራ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል፡፡ የጎንደር ዩንቨርሲቲ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ ተከተል ዮሀንስ (ፕ/ር) በበኩላቸውን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሚነሱ አበይት ችግሮች መካከል የትምህርት ጥራት ዋነኛ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። ለትምህርት ጥራት ስኬት ከታች ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ተገቢና በቂ ትምህርት እያገኙ እንዲያድጉ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ የሚስተዋለውን የጥራት ችግር ለመፍታት የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ። የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ ከተመደቡት የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች…

በአምባሰል ወረዳ ራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በተለምዶ ራስ ጠቆሮ እየተባለ በሚጠራ ጥብቅ ደን ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለፀ፡፡ የእሳት አደጋው ከሰኔ 6 ቀን 2014ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ የተከሰተ መሆኑ እና እስካሁን ድረስ…

“ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የድብቅ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰላም ሂደቱን በተመለከተ የሚያጠና ኮሚቴ መዋቀሩን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ሰኔ 07/2014 ዓ. ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ…

ታጣቂዎች የጋምቤላ ከተማን በከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረ ክልሉ ገለጸ

ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ላይ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ጥቃት ከፍተው የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበረ የክልሉ መንግሥት ገለጸ። የክልሉ መስተዳደር ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በጋምቤላ ከተማ “የሸኔ እና የጋምቤላ…

አብን 40 አመራሮቹ እና አባሎቹ እንደታሰሩበት ገለጸ ከ 20 በላይ ጋዜጠኞች መታሰራቸውም ተገልጿል

በ”ሕግ ማስከበር ሽፋን” ሕፃናትን ጨምሮ 35 ዜጎች ያለፍ/ቤት በፀጥታ ሃይሎች መገደላቸውንም ገልጸዋል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መንግስት ሕግ የማስከበር ስራ ባለው ዘመቻ 40 አባሎቹና አመራሮቹ እንደታሰሩበት አስታወቀ፡፡ የንቅናቄው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና…

መንግስት በፍራንኳ ቫሉታ ምክንያት 33 ቢሊዮን ብር ማጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ

የግብርና ስራዎችን ለማሻሻል በሚል መንግስት ለግል ባለሀብቱ 73 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱንም ገልጿል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያሉት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው መንግስት…

ኢትዮጵያ በሀገራት መካከል ሰላም እንዲኖር አበክራ ትሰራለች – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ኢትዮጵያ በሀገራት መካከል ሰላም እንዲኖር አበክራ ትሰራለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባለት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ኢትዮጵያውያን ሰላም ወዳድ መሆናችንን ዓለም መስክሯል ብለዋል…

ዶክተር ይልቃል የወልቃይት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ እንደሆነ በጎንደር በተደረገ ህዝባዊ ውይይት አረጋገጡ

ስለወልቃይት ጉዳይ ብዙ ሲባል ሰንብቷል፤ አንዱ የክልሉ የህግ ማስከበር ዘመቻ ዓላማው ወልቃይትን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ መደላድል ለመፍጠር ነው የሚሉም አሉ፡፡ የክልሉ መሪ ዶክተር ይልቃል ከፍ ያለ ደግሞ የሚባለው ሁሉ ይባላል፡፡…

በዩክሬን ሉሃስክ ክልል የሚገኙ 284 ሺህ ነዋሪዎች የሩሲያ ዜግነት መቀበላቸው ተገለፀ

ሩሲያ በያዘቻቸው የዩክሬን ከተሞች ፓስፖርት መስጠት መጀመሯ ይታወቃል ዩክሬን “ሩሲያ እያደረገችው ያለው ተግባር በግዛቴ ውስጥ የሩሲያ ዜጎች መፈጠር ነው” ብላለች በዩክሬኗ ሉሃንስክ ግዛት ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የሩሲያን ዜግነት…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም የአገራቱን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ በተለይም በሀገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው…

ፑቲን፣ ‘ምዕራቡ ዓለም ያለኛ የኃይል አቅርቦት ብዙም አይዘልቅም’ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን ምዕራቡ ዓለም የለ አገራቸው የኃይል አቅርቦት ብዙም አይዘልቅም ሲሉ ተናገሩ።

ፑቲን ይህን ያሉት የአሜሪካ ባለሥልጣናት የሩሲያ ነዳጅና ጋዝ አቅራቢ ኩባንያዎችና አገሪቱ ማዕቀብ ከተጣለባት በኋላ የበለጠ አትራፊ እየሆኑ መምጣታቸውን ባመኑ ማግስት ነው። የአውሮጳ ኅብረት አሁን ላይ 40 ከመቶ የሚሆነውን የጋዝ ፍላጎቱን…

በአፋር ክልል ከ1.3 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ለምግብ እጥረት መጋለጡ ተገለጸ በአፋር ክልል በጦርነት እና በተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለምግብ እጥረት መጋለጡ ተገለጸ።

የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ጦርነት ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብን ለከፋ የምግብ እጥረት አጋልጧል። ትናንት ሰኔ…

ትራምፕ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ክስ ቀረበባቸው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተከሰሱ።

ትራምፕ ከአንድ ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ የካፒቶል ሂል አመጽን አቀነባብረዋል ተብለዋል። ይህ የቀድሞ ፕሬዝደንት ላይ የቀረበው ክስ የተሰማው ኮንግረሱ የካፒቶል ሂል ሁከትን መመርመር በመጀመረበት ጊዜ ነው። ከአንድ ዓመት በፊት…

ሞዛምቢክ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሆነች

ሞዛምቢክ 192 የፀጥታው ምክር ቤት አባላትን ድምፅ በማግኘት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሆናለች፡፡ ከሞዛምቢክ በተጨማሪ ኢኳዶር፣ጃፓን፣ ማልታ እና ስዊዘርላንድ ትላንት በተደረገው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ምርጫ የአባልነት…

ተመድ ተፈጸሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ሊያደርገው ያቀደው ተጨማሪ ምርመራ ተቀባይነት የለውም – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ተመድ ተፈጸሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ሊያደርገው ያቀደው ተጨማሪ ምርመራ ተቀባይነት እንደሌለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በኢትዮጵያ…

ዘሌንስኪ፤ የዩክሬን ኃይሎች በሩሲያ ኃይሎች ላይ ከባድ ወታደራዊ ኪሳራ እያደረሱ መሆናቸውም ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጅ የዩክሬን ኃይሎች በሩሲያ ኃይሎች ተገፍተው ከተማዋ ለቀው ለመውጣት እየተገደዱ እንደሆን ፍራንስ-24 ዘግቧል፡፡ የሉሃንስክ ግዛት አስተዳዳሪ ሰርሂ ሀዳይ በበኩላቸው፤ የሩሲያ ኃይሎች በአውሮፕላን እና ከባድ መሳሪያዎች መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘራቸውንና…

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ግንባታን አጠናቆ ሊያስመርቅ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ፕሮጀክቱ አሉሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ” የተሰኘ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ያዋለ ሲሆን÷ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች…

This site is protected by wp-copyrightpro.com